ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ዛሬ ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ጋር በዋና ዋና የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርጌያለሁ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ረጅም ታሪክ እና ጥልቅ ግንኙነት እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯ ጉብኝትም ይሄንን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ነው ያሉት፡፡
ወደፊት ስንመለከት፣ አጋርነታችን ከፖለቲካ እና ከዲፕሎማሲ በላይ በመስፋፋት ከፍተኛ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብርን ይጨምራልም ብለዋል፡፡