Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው እድገት የዓለም የንግድ ድርጅትን  እንድትቀላቀል በር ከፋች ነው ተባለ

 

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው የኢኮኖሚ እድገት የዓለም የንግድ ድርጅትን  እንድትቀላቀል በር ከፋች መሆኑ ተገለፀ፡፡

 

የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ዋና ተደራዳሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት ተደራዳሪ ኮሚቴ አባላት ከዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ጋር ተወያይተዋል።

 

በውይይቱ  ሚኒስትሩ ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ÷እያደገ ለመጣው የኢኮኖሚ እድገት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ተናግረው ይህም ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅትን ሁለት ዓመት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ እንድትቀላቀል አስተዋፅዖዉ የጎላ ነዉ ብለዋል፡፡

 

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ንጎዚ ኦኮንጆ ÷ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ምቹ መደላድል የፈጠረች ሀገር መሆኗን አንስተው እንደ አብነትም ዳንጎቴ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ሁለተኛ ምዕራፉን እያሰፋ መምጣቱ አንዱ ማሳያ መሆኑን መናገራቸውን ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

 

ኢትዮጵያ እያካሄደችዉ ላለዉ ተጨባጭ የኢኮኖሚ እድገት  የዓለም የንግድ ድርጅት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

 

በአመለወርቅ መኳንንት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.