ዓለም ባንክ ዘመናዊ የትራፊክ ስርዓት ዝርጋታ ስራን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑን ገለፀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣናዊ ምክትል ፕሬዚዳንት ከሆኑት ቪክቶሪያ ኳኳ (ዶ/ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ፕሬዚዳንት ቪክቶሪያ ኳኳ (ዶ/ር)÷ በሰው ተኮር ስራ፣ በምገባ መርሐ ግብር፣ በሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ፈጣን ለዉጦች ተመዝግበዋል ማለታቸውን ከንቲባ አዳነች በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል፡፡
በከተማ ንፅህና አጠባበቅ እና ፍሳሽ አወጋገድ እንዲሁም የትራፊክ መጨናነቅን ለመቀነስ የተጀመረው ዘመናዊ የትራፊክ ስርዓት ዝርጋታ ስራ የሚበረታታ ስለመሆኑ መግለጻቸውን አንስተዋል፡፡
ለዚህም አለም ባንክ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ቪክቶሪያ ኳኳ (ዶ/ር) መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡