Fana: At a Speed of Life!

ቀነኒሳ በቀለ በ2025 የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት 2025 በሚካሄደው የለንደን ማራቶን እንደሚሳተፍ አስታውቋል፡፡

በ40 ዓመት ዕድሜ ላይ የሚገኘው አትሌት ቀነኒሳ የለንደን ማራቶን የመጨረሻው ዓለም አቀፋዊ ውድድር ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል፡፡

በለንደን ማራቶን በድጋሚ እንደሚሳተፍ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያረጋገጠው አትሌት ቀነኒሳ÷ በሩጫ ሕይወቱ ከጎኑ ላሉ አድናቂዎቹ እና ቤተሰቦቹ ምስጋና አቅርቧል፡፡

በአትሌቲክስ ዘርፍ ለ22 ዓመታት መቆየት የቻለው ወርቃማው አትሌት 3ኛው የማራቶን ፈጣን ሰዓት ባለቤት ሲሆን÷በ2024ቱ የለንደን ማራቶን በመሳተፍ በ40 ዓመቱ ማራቶን መሮጥ የቻለ የመጀመሪያው አትሌት መሆን ችሏል፡፡

በውድድሩ የቀነኒሳ የ22 ዓመታት ተቀናቃኝ የነበረው ኬኒያዊው አትሌት ኤሊዩድ ኪፕቾጌ ይሳተፋል መባሉንም የለንደን ማራቶን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.