በአፍሪካ ህብረት ጉባዔ የተሳተፉና የቆይታ ጊዜያቸውን ያራዘሙ መሪዎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉ እና የቆይታ ጊዜያቸውን ያራዘሙ መሪዎች ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው።
በዚህም የቦትስዋና ፕሬዚዳንት ዱማ ቦኮ እና የካሜሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆሴፍ ጀን ጉቴ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ለመሪዎቹ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች በቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አሸኛኘት ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።