ለብሔራዊ ጥቅም መከበር የሚሠራ ኮሚሽን ማቋቋም እንደሚገባ ተመላከተ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መከበር የሚሠራ እና ጉዳዩን በኃላፊነት የሚከታትል ኮሚሽን ማቋቋም እንደሚገባ ተገለጸ።
“ሀገራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጣናዊ ትስስር ለሕዝቦች ሚዛናዊ ተጠቃሚነት” በሚል ርዕስ የሰላም ሚኒስቴር እና ጅማ ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጁቱ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጀማል አባፊጣ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ ለፍትሐዊ ተጠቃሚነት መረጋገጥ፣ በቀጣናና በዓለም አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ ጥቅሞች እንዲጠበቁ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማኅበረሰብ ተሳትፎ ሚና የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለ ግንኙነትን እና ቀጣናዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚገባ የውይይት ጽሑፍ ያቀረቡት የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ኢድሪስ የባ (ዶ/ር) ጠቁመዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መከበር የሚሠራ እና ጉዳዩን በኃላፊነት የሚከታትል እራሱን የቻል አንድ ኮሚሽን ማቋቋም እንደሚገባም ነው ያመላከቱት፡፡
በወራቃፈራው ያለው