Fana: At a Speed of Life!

አሥተዳደሩ ያስገነባቸውን 192 የመኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች አስተላለፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በበጎነት የመኖሪያ መንደር ለአቅመ ደካሞች እና የልማት ተነሺዎች ያስገነባቸውን 192 የመኖሪያ ቤቶች ለነዋሪዎች አስረክቧል፡፡

የአሥተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ 192 የመኖሪያ ቤቶችን የያዙ ሁለት ባለ 9 ወለል ሕንጻዎች ለነዋሪዎች ዛሬ ማስተላለፋቸውን አስታውቀዋል፡፡

የመኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የሕጻናት መጫወቻ፣ የእንጀራ መጋገሪያ ፋብሪካ፣ የጸጉር እና የልብስ ስፌት የሥራ ዕድሎች የተካተቱበት፣ የዜግነት ክብርን የሚመጥን፣ ንፁህ እና ውብ አካባቢን ለነዋሪዎች አስረክበናል ብለዋል፡፡

ድጋፍ ላደረገው የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራሮቹ እና ሰራተኞችም ከንቲባዋ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.