Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ ፌዴራል ጉባኤ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

በአፈ ጉባኤዋ የተመራዉ ልዑክ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ፣ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በሁለት ቀናት የኢትዮጵያ ቆይታው ከተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ የሚመክር ሲሆን በአዲስ አበባ የሚገኙ ታሪካዊ ቦታዎችንም ይጎበኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.