Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሰላምን ለማስፈን ለምታደርገው ጥረት አውሮፓ ህብረት ድጋፉን እንደሚያጠናክር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምን ለማስፈን ለምታደርገው ጥረት የአውሮፓ ህብረት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ(ኢ/ር) በአውሮፓ ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ አኔት ዌበርን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን÷ በተለይም በሶማሊያና በኢትዮጵያ መካካል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል እየተከናወኑ ያሉ ጥረቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራዊና ክልላዊ ሰላምን ለማስፈን ለምታደርገው ጥረትም የአውሮፓ ህብረት ድጋፉን እንደሚቀጥል ልዩ ተወካይዋ ማረጋገጣቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.