Fana: At a Speed of Life!

በሻምፒየንስ ሊግ ሪያል ማድሪድ ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ሲከናወኑ ሳንቲያጎ ቤርናባው ላይ ሪያል ማድሪድ ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡

ኤቲሃድ ስታዲየም ላይ በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ሪያል ማድሪድ 3 ለ 2 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ምሽት በውድድሩ ለመቆየት የሚደረገው የሁለቱ ኃያላን ክለቦች ተጋድሎ ይጠበቃል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ ኒውካስል ዩናይትድን 4 ለ 0 ማሸነፉ ለዛሬው ጨዋታ መነቃቃትን እንደሚፈጥርለት ተነግሯል፡፡

በጥር የዝውውር መስኮት ማንቼስተር ሲቲን የተቀላቀለው የመሃል ሜዳው ተጨዋች ኒኮ ጎንዛሌዝ ባለፈውን ጨዋታ በብቃት መወጣቱ ሲቲዎች የዛሬውን ጨዋታ ለማሸነፍ ተስፋ እንዲያደርጉ ረድቷቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ግብጻዊው ኦማር ማርሙሽ ያሳየው አስደናቂ አጀማመር ማንቼስተር ሲቲ የአሸናፊነት ግምት እንዲያገኝ አድርጓል፡፡

በተከላካይ መስመር ተጨዋቾች ጉዳት እየታመሰ ለሚገኘው ሪያል ማድሪድ አንቶኒዮ ሩዲገር ከጉዳት መልስ በዛሬው ጨዋታ ይሰለፋል ተብሏል፡፡

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ የሚከናወን ሲሆን÷ በተመሳሳይ ሰዓት ፒኤስጂ ከብረስት እንዲሁም ፒኤስቪ ከጁቬንቱስ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ቀደም ብሎ ምሽት 2 ሰዓት ከ45 ሲል ቦሩሺያ ዶርቱመንድ ከስፖርቲንግ ሊዝብን የሚጫወቱ ይሆናል፡፡

ትናንት ምሽት የመድረኩ የመልስ ጨዋታዎች የተደረጉ ሲሆን ፌይኑርድ ኤሲሚላንን በደርሶ መልሰ 2 ለ 1፣ ክለብ ብሩጅ አታላንታን 5 ለ 2፣ ባየርንሙኒክ ሴልቲክን 3 ለ 2 እንዲሁም ቤኔፊካ ሞናኮን 4 ለ 3 በሆነ ድምር ውጤት በማሸነፍ 16ቱን ተቀላቅለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.