Fana: At a Speed of Life!

እንግሊዝ 12 አምቡላንሶችን ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስረከበች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር በሀገሪቱ መንግሥት የተራድኦ ድርጅት የተገዙ 12 አምቡላንሶችን ለኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር አስረክበዋል።

አምቡላንሶቹን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ፕሬዚዳንት አበራ ቶላ ከእንግሊዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አንጄላ ሬይነር ተረክበዋል።

አምቡላንሶቹ ለእናቶችና ህፃናት ፈጣንና የተሻለ የጤና ሰብዓዊ አገልግሎት የሚሰጡና የተሟላ የሕክምና ቁሳቁስ እንዳላቸው ተገልጿል።

አንጄላ ሬይነር እና ልዑካን ቡድናቸው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር እያከናወናቸው የሚገኙ የሰብዓዊ ተግባራትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ከማኅበሩ አመራሮች ጋርም በቀጣይ በትብብር በሚሰሯቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.