የካቲት 12 ዘመን ተሻጋሪ ፅናታችንን የምናስብበት ነው- ፕሬዚዳንት ታዬ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የካቲት 12 ለሀገራችን ያለንን ፍቅር እና ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ፅናታችንን የምናሳይት ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የካቲት 12 የመስዋዕታችንን ፋይዳ የምናስብበት ዕለት ነው ብለዋል፡፡
የካቲት 12 የሰማዕታት ቀን የኢትዮጵያውያን የፀረ-ቅኝ ግዛት ተጋድሎ፣ ለነፃነት ያለን ቀናኢነት፣ ለሀገራችን ያለንን ፍቅር፣ ዘመን ተሻጋሪ የሆነውን ፅናታችንና የመስዋዕታችንን ፋይዳ የምናስብበት ዕለት ነው ሲሉም ገልጸዋል