Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ በኢትዮጵያ የሩሲያ ቋንቋ ት/ቤቶችን ለመክፈት ማቀዷን ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሩሲያ በኢትዮጵያ የሩሲያ ቋንቋ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት እቅድ እንዳላት የሀገሪቱ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊቀመንበር ሚስዝ ቫለቲና ማትቬንኮ ገለጹ፡፡

ሊቀመንበሯ ይህንን ያሉት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በመከሩበት ወቅት ነው፡፡

በውይይታቸውም ሚስዝ ቫለቲና ማትቬንኮ የሩሲያና የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ዘመናትን የተሻገረ እና በአፍሪካ በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በርካታ የጋራ እሴቶች ያሏቸው፣ በኢኮኖሚ የተሳሰሩ፣ ጠንካራ ፓርላሜንታዊ ግንኙነት የመሠረቱ እና በጂኦፖለቲካዊ ሁኔታዎች የማይናጋ የጋራ አቋም የሚያራምዱ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ሀገራቱ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉ መሆናቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳል አመራርነት ኢትዮጵያ በአፍሪካ መድረክ ከፍ ብላ እየታየች መሆኗንም አውስተዋል፡፡

በቀጣይም ሩሲያ በልማት፣ በኢንቨስትመንት፣ በኅብረተሰብ ጤና እና በትምህርት ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.