Fana: At a Speed of Life!

አርጀንቲና ከኢትዮጵያ ጋር በትምህርት ዘርፍ የመሥራት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርጀንቲና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር በማሳደግ በትምህርት ዘርፍ በጋራ የመሥራት ፍላጎት እንዳላት አስታውቃለች፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በኢትዮጵያ የአርጀንቲና አምባሳደር ኢግናሲዮ ሮካታግሊታ ጋር በትምህርት ዘርፉ በትብብር በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በዚሁ ወቅትም ሀገራቱ በሚኖራቸው ትብብር በትምህርት ዘርፍ ሊሠሩባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲዎች ጋርም በትብብር መሥራት የሚቻልበት ምቹ ሁኔታ አለ ማታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

አምባሳደሩ በበኩላቸው÷ አርጀንቲና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር በማሳደግ በትምህርት ዘርፍ በጋራ መሥራት እንደምትፈልግ አረጋግጠዋል፡፡

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችና መምህራን ልውውጥና ነጻ የትምህርት እድል፣ በአዳዲስ ፈጠራዎች፣ በኪነ ጥበብ፣ ስፖርት እንዲሁም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በሚያጠናክሩ ተግባራት ላይ በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.