የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ መሰረት የዓድዋ ድል ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ መሰረት የዓድዋ ድል ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ገለጹ።
አምባሳደር ነብያት ከፋና አንድ ጉዳይ ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ ኢትዮጵያ በዓድዋ ድል ነጻነቷን መጎናጸፏ የዓለምና አህጉር አቀፍ ተቋማት መስራች ሀገር እንድትሆን ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
የዓድዋ ድል በቅኝ ግዛት ስር ለነበሩ ሀገራት የነጻነት እና የፓን አፍሪካኒዝም መነሻ መሆኑንም ነው ያወሱት፡፡
ብዙ ዋጋ የተከፈለበት ዓድዋ ከኢትዮጵያ አልፎ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ መሆኑን ገልጸው÷ ዓድዋ ድልን የበለጠ ለሀገር ገጽታ ግንባታ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዛሬም ድረስ የኢትዮጵያዊያን አልበገር ባይነት ቋሚ ማስታወሻ ነው ሲሉም አምባሳደር ነብያት ገልጸዋል፡፡
በመሳፍንት እያዩ