Fana: At a Speed of Life!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ3 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አጸደቀ

 

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት ከ3 ቢሊየን በላይ  ብር ተጨማሪ በጀት አፅድቋል፡፡

 

የምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

 

በጉባኤው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን መሰረተ ልማት እና የመንግስት ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ የተጨማሪ በጀት ረቂቅ በዝርዝር አቅርቧል፡፡

 

በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ከምክር ቤቱ አባላት እና ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ማብራሪያ ተሰጥቷል።

 

ይህን ተከትሎም ምክር ቤቱ በሁለተኛ ቀን ውሎው የ2017 በጀት ዓመት 3 ቢሊየን 120 ሚሊየን 374 ሺህ 10 ብር ተጨማሪ በጀት መርምሮ አጽድቋል።

 

ተጨማሪ በጀቱ ለክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት፣ለዞኖች እና ለልዩ ወረዳዎች፣ለደመወዝ ማስተካከያ እና ለኑሮ ውድነት መደጎሚያ የሚውል ነው መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.