በኢኮኖሚ ዞኑ ከ160 ሚሊየን ዶላር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የማሽን ተከላ ስራ ጀመሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ከ160 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 6 ባለሃብቶች ምርት ማምረት የሚያስችላቸውን የሼድ ግንባታና ማሽን ተከላ ስራ ማከናወን ጀምረዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)÷ በኢኮኖሚ ዞኑ ምርት ለማምረት በሒደት ላይ ያሉ ባለሃብቶችን የስራ እንቅስቃሴተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ባለሃብቶቹ በተያዘው በጀት ዓመትና በ2016 በጀት ዓመት መጨረሻ ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ስራ ለመጀመር ስምምነት ተፈራረመው ወደ ስራ መግበታቸው ተገልጿል፡፡
አሁን ላይም ምርት የማምረት ስራ መጀመር የሚያስችላቸውን የሼድ ግንባታና የማምረቻ ማሽን ተከላ ስራ በማከናወን ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
ባለሃብቶቹ ወደ ስራ ሲገቡም ከ2 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡