የሩሲያ ፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሩሲያ ፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ቫለቲና ማትቬንኮ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ለአፈ-ጉባዔዋ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።
ቫለቲና ማትቬንኮ በኢትዮጵያ ባካሄዱት የሥራ ጉብኝት በእጅጉ መደሰታቸውንና የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጠንካራና የማይናጋ ሆኖ እንዲቀጥል የሚያስችሉ ሁኔታዎችን መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቆይታቸው ለተደረገላቸው መስተንግዶ እና አቀባበል ምስጋና ማቅረባቸውንም የምክር ቤቱ መረጃያመላክታል፡፡
አፈ-ጉባኤ አገኘሁ በበኩላቸው÷በሩሲያ እና ኢትዮጵያ መካከል ለረጅም ዘመናት ጸንቶ የቆየው መልካም ዲፕሎማሲያዊ አጋርነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡