Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ

 

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከእንግሊዝ የቀይ ባሕር እና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አሊሰን ብላክበርን ጋር ተወያይተዋል።

 

በውይይታቸው በኢትዮጵያ እና በእንግሊዝ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ባለብዙ ወገን የጋራ ፍላጎቶች የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

 

የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት በምጣኔ ሀብት ትስስር፣ በፖለቲካ ምክክር እና በሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት መንገድ ላይ ሐሳብ መለዋወጣቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

 

እንዲሁም ኢትዮጵያ እና እንግሊዝ በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው መስኮችም መወያየታቸው ተገልጿል።

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.