ፌደራል ፖሊስ በፎረንሲክ ምርመራ ከ358 ሰነዶች ውስጥ 73 በመቶዎቹ ሀሰተኛ መሆናቸውን አረጋገጠ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ358 ሰነዶችን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ባካሄደው የፎረንሲክ ምርመራ 73 በመቶዎቹ ሀሰተኛ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡
ተቋሙ ባለፉት 6 ወራት 191 የወንጀል ጉዳዮች እና 167 ከፍታብሔር ጋር የተያያዙ የምርመራ ጥያቄዎችን ከፖሊስና ፍርድ ቤት መቀበሉን ገልጿል፡፡
ፌደራል ፖሊስ በ358 ሰነዶች ላይ ባካሄደው የፎረንሲክ ምርመራም 73 በመቶ የሚሆኑት ሃሰተኛ መሆናቸውን ነው ያረጋገጠው፡፡
የፌደራል ፖሊስ የተለያዩ የወንጀልና የፍታብሔር ጉዳዮችን በዘመናዊ የፎረንሲክ ምርመራ ላብራቶሪ መሣሪያዎች በሚገባ እየመረመረ ውጤቱን ለሚመለከተው አካል እየሰጠ እንደሚገኝም አመላክቷል፡፡