Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር እሸቴ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኔዘርላንድስ ንጉስ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኔዘርላንድስ የኢትዮጵያ አምባሳደር እሸቴ ጥላሁን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኔዘርላንድስ ንጉስ ዊሌም አሌክሳንደር አቅርበዋል።

በዚህ ወቅትም አምባሳደር እሸቴ ከንጉስ ዊሌም አሌክሳንደር ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ ወገኖች ሀገራቱ ያላቸውን ጥብቅ ትስስር አጠናክሮ ለማስቀጠል በጋራ መስራት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

አምባሳደር እሸቴ በኔዘርላንድስ በሚኖራቸው ቆይታ የሀገራቱን የንግድና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከር እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፍና በሌሎች መስኮች ላይ በሰፊው እንደሚሰሩ ለንጉሱ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ንጉስ ዊሌም አሌክሳንደር በበኩላቸው ለአምባሳደር እሸቴ መልካም ምኞታቸውን በመግለጽ፤ኢትዮጵያ እና ኔዘርላንድስ በተለያዩ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች የረጅም ጊዜ ትብብር እንዳላቸው አንስተዋል፡፡

ኔዘርላንድስ በቀጣይ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ማረጋገጣቸውንም የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.