Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 2ኛው የተባበሩት መንግስታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ ለማስተናገድ ዝግጅት እያደረገች መሆኑን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመጪው ሐምሌ ወር በአዲስ አበባ የሚካሄደውን 2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ስርዓት ጉባዔ ለማስተናገድ በተጀመሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በውይይቱ ላይ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በምግብ ራሰን ለመቻል እየተደረጉ ያሉ ተግባር ተኮር እና ለውጥ ያመጡ ሥራዎችን በተመለከተ ገለፃ ሰጥተዋል።

በተቀናጀ መልኩ ቀጣዩን ጉባኤ ለማስተናገድ ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በበኩላቸው ÷ በቀጣይ ሐምሌ ወር ለሚካሄደው ጉባኤም ኢትዮጵያ ያላትን አቅም በመጠቀም የተሟላ ዝግጅት እንደምታደርግ መናገራቸውን የሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የልዑካን ቡድን መሪ እስጢፋኖስ ፎሽው(ዶ/ር) ÷ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተከናወነ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎች በማድነቅ ኢትዮጵያ ቀጣዩን ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ እንደምታስተናግድ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በጉባኤው የቅድመ ዝግጅት የኮሚቴ ውይይት ባለድርሻ አካላት እና በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽ/ቤት አምባሳደሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.