ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ኮሚሽን ም/ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) ከአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ካጃ ካላስ ጋር በጆሃንስበርግ ተወያይተዋል፡፡
ከቡድን 20 የሚኒስትሮች ጉባኤ ጎንለጎን በተደረገው ውይይት ሁለቱ ወገኖች በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ጠንካራ እና ዘላቂ ግንኙነትን ለመፍጠር ቁርጠኛ መሆኗን መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡