የማህበረሰባችንን ጥያቄ ለመመለስ ይበልጥ እንተጋለን – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማህበረሰባችንን ጥያቄ ለመመለስ ይበልጥ እንተጋለን ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት ከሕዝብ በሚቀርቡ ቅሬታና አቤቱታዎች እንዲሁም በየደረጃው የተሰጡ ምላሾችን በሚመለከት ከክልል እና ፌደራል ተቋማት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
ውይይቱ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በሱፐርቪዥን በማረጋገጥ የቀጣይ የትኩረት መስኮች ላይ ማህበረሰቡን ጥያቄ መመለስ በሚያስችሉ አሰራሮች ዙሪያ ግብረ መልስ ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዚህ ወቅትም በቀጣይ የማህበረሰቡን ጥያቄ ለመመለስ በይበልጥ በትጋት እንደሚሰራ ነው የተመላከተው፡፡