ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፈረንስ ከነገ ጀምሮ በ25 ከተሞች ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፈረንስ ከነገ ጀምሮ በ25 ዋና ዋና ከተሞች መካሄድ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡
ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፍረንሱ በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ም/ቤት አባላት የሚመራ መሆኑን የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህ መሰረትም ኮንፍረንሱን የሚመሩ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና ም/ቤት አባላት ወደ ተለያዩ ከተሞች እየገቡ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡