በመዲናዋ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።
ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፈረንስ ከዛሬ ጀምሮ በ25 የኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች እንደሚካሄድ የብልጽግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል።
በዚህም መሠረት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ ዜጎች የተሳተፉበት የህዝብ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
መድረኩን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አለሚቱ ኡሞድ እና የብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እየመሩት ይገኛሉ፡፡