በወላይታ ሶዶ የሕዝብ ኮንፈረንስ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ኦርዲን በድሪ፣ የአማራ ክልል ም/ርዕሰ መሥተዳደርና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አብዱ ሁሴን(ዶ/ር) እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
መድረኩ በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች እንዲሁም በልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ ከከተማው ህዝብ ጋር ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡፡
በዚህም ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች ለሚነሱ ጥያቄዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚና የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጥላሁን ሁሴን