በጅማ ከተማ የህዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጅማ ከተማ የህዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
በኮንፈረንሱ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነመራ ቡሊና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
እንዲሁም ከጅማና ቡኖ በዴሌ ዞኖች የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች በመድረኩ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)÷ብልጽግና ፓርቲ ከገጠሙት ችግሮች እየተማረ የያዛቸውን እቅዶች እያሳካ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
ፓርቲው በ2ኛው መደበኛ ጉባዔ ላይ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎች እውን ለማድረግ አበክሮ እንደሚሰራም አስገንዝበዋል፡፡
በአብዱራህማን መሃመድ