Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በጎንደር ከተማ የህዝብ ኮንፈረንስ መካሄድ ጀምሯል።

በኮንፈረንሱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ደኘው ተገኝተዋል፡፡

እንዲሁም የሐይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ እንደሚገኙ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

በመድረኩ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች እንዲሁም በልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.