በሸገር ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሸገር ከተማ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ የሕዝብ ኮንፈረንስ መካሄድ ጀምሯል።
በኮንፈረንሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ሃላፊ መሠረት አሰፋና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም ከሸገር ከተማ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡