Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ከተማ የህዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር ማስረሻ በላቸው፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

በህዝባዊ ኮንፈረንሱ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ በተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

በኮንፈረንሱ ከህብረተሰብ ለሚነሱ ጥያቄዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚና የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመላክቷል፡፡

በተሾመ ሃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.