Fana: At a Speed of Life!

በደሴ ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደሴ ከተማ ”ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር)፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማእረግ የኦሮሚያ ክልል የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ሳዳት ነሻ እንዲሁም ሌሎች የክልልና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል።

የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ ፥ በደሴ ከተማ አመራሩ በቅንጅት ማህበረሰቡን አሳትፎ የሰራቸው የልማት ስራዎች ከዚህ በፊት ሲነሱ ለነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይ ሰላም ወዳድ የሆነውን የደሴ ከተማ ማህበረሰብ በማሳተፍ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን አጠናክረን እናስቀጥላለን ሲሉም ቃል ገብተዋል፡፡

በእሸቱ ወ/ሚካኤል

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.