አርሰናል ከዌስትሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
በውጤት እጦት ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ ቀን 9:30 ከሜዳው ውጭ ኤቨርተንን ይገጥማል።
አርሰናል ከመሪው ሊቨርፑል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ምሽት12 ሰዓት ላይ ዌስትሃም ዩናይትድን በኢምሬትስ የሚያስተናድበት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ኢፕስዊች ታውን ከቶተንሃም፣ ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ፣ ቦርንማውዝ ከወልቭስ እንዲሁም ሳውዛምፕተን ከብራይተን በተመሳሳይ 12 ሰዓት ላይ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።
ምሽት 2:30 ደግሞ ቼልሲ ወደ ቪላ ፓርክ አቅንቶ አስቶን ቪላን የሚገጥምበት ጨዋታ ብርቱ ፉክክር ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
ትናንት ምሽት በተደረገው የ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ሌስተር ሲቲ በሜዳው በብሬንትፎርድ 4 ለ ዐ በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፏል።