ከማሕበረሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረትና በትብብር ይሰራል – አቶ ደስታ ሌዳሞ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከማሕበረሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት በትኩረትና በትብብር ይሰራል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡
ከአዳማ ከተማ፣ ከምስራቅ ሸዋ እና አርሲ ዞኖች የተውጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ የህዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ በብልጽግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ የተቀመጡ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች እንዲሁም በልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል ፡፡
አቶ ደስታ ሌዳሞ በዚህ ወቅት ፥ ብልጽግና ፓርቲ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም በርካታ ለውጦችን እያስመዘገበ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ዕድል እና የጋራ ቤት ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፓርቲው በሁለተኛው መደበኛ ጉባዔው ያስቀመጣቸው ውሳኔዎች የመንግስት እቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑ አንስተዋል ።
በቀጣይ በሰላምና ደህንነት፣ በኑሮ ውድነት፣ በስራ አጥነት፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እና በሀገር ግንባታ ስራዎች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡
መንግስት ከዜጎች የሚነሱ ጥያቄዎችን እንዲፈታ ሕብረተሰቡም የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
በፈትያ አብደላ እና መሳፍንት እያዩ