Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር በኦንላይን የጉዞ ትኬት መቁረጥ የሚያስችል አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ለመንገደኞች የጉዞ ትኬት በኦንላይን መቁረጥ የሚያስችል አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ከፈረንጆቹ የካቲት 24 ቀን 2025 ጀምሮ መንገደኞች ብሔራዊ መታወቂያን በመጠቀም በኦንላይን ቦታ ማስያዝና የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ዲጂታላይዝድ መሆኑን ጠቅሰው÷ ይሄም ጥራት ያለውና እና ቀልጣፋ የጉዞ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡

የዲጂታል አገልግሎት ስርዓቱን የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ከኢትዮ ቴሌኮምና ብሔራዊ መታወቂያ ጋር በትብብር ማዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.