Fana: At a Speed of Life!

አቶ አደም ፋራህ በአክ ፓርቲ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አንካራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በአክ ፓርቲ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ቱርክ አንካራ ገብተዋል።

በስፍራው ሲደርሱም የአክ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች እና በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሀመድን ጨምሮ ሌሎች የኤምባሲው የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፓርቲው ከነገ ጀምሮ ጠቅላላ ጉባዔውን የሚያደርግ ሲሆን÷ብልፅግና ፓርቲም ከፓርቲው በቀረበለት የተሳትፎ ግብዣ መሰረት አቶ አደም ፋራህን በመወከል በጉባዔው ላይ ተሳትፎ ያደርጋል።

ባለፈው ወር በአዲስ አበባ በተካሄደው የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የቱርኩ አክ ፓርቲ የፓርቲውን ምክትል ፕሬዚዳንት ዛፈር ሲራካያ በመወከል መሳተፉንም የብለፅግና ፓርቲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከጉባዔ ተሳትፎ በተጨማሪም ፓርቲዎቹ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

የሁለቱ ፓርቲዎች ግንኙነት ቀደም ሲል በኢትዮጵያና ቱርክ መንግስትና ህዝቦች ህዝቦቸመካከል የነበረውን ዘመን የተሸገረ ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.