Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከቡና የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር ውጤት እያመጣች ነው – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የቡና አምራች ሀገር እንደመሆኗ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ ሰፊ የሪፎርም ስራዎችን በመተግበር ውጤት እያመጣች ትገኛለችም ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ኮፊ አረቢካን ጨምሮ ዓለም ላይ ተፈላጊ የሆነ ባለ ልዩ ጣዕምና ጠንካራ የቡና ምርት መገኛው በአህጉራችን አፍሪካ ነው ብለዋል፡፡

በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከተማ የተካሄደው 3ኛው የቡድን-25 (G25) የአፍሪካ የቡና ጉባኤ የአህጉሩን የቡና አቅም የሚያሳድጉ ምርምሮችና ትብብሮችን የሚያጠናክሩ ውሳኔዎች አሳልፈናልም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

”የአፍሪካ የቡና ኢንዱስትሪን በማነቃቃት ለወጣቶች የሥራ ዕድሎችን መክፈት” በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደውው ጉባዔ ዘርፉን ለማነቃቃትና ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረናል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በጉባኤው ባቀረበችው ጥያቄ መሰረት አራተኛውን የቡድን – 25 የአፍሪካ የቡና ጉባኤ በ2019 ዓ.ም በኢትዮጵያ እንዲካሄድ መወሰኑንም አንስተዋል፡፡

ለኢትዮጵያ የተሰጠውን ዕድልም በታላቅ ኃላፊነት ተቀብለናል ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.