Fana: At a Speed of Life!

በረሃማ አካባቢዎችን ለማልማት የጥናትና ምርምር ስራዎች መንገድ አመላካች ናቸው ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በረሃማና ከፊል በረሃማ አካባቢዎችን ለማልማትና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በዘርፉ የሚደረጉ የጥናትና ምርምር ስራዎች መንገድ አመላካች መሆናቸው ተመላከተ፡፡

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ ” ተግባራዊ እውቀትን ለአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ለውጥና ጥቅም ላይ ማዋል” በሚል መሪ ሃሳብ እያካሄደ ነው፡፡

በዚሁ ወቅት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት፣ ስራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሬ ሌንጮ(ዶ/ር)÷በአፍር ክልል ያሉ ብዝሀ የተፈጥሮ ሀብቶችን በጥናት ምርምር በመደገፍ ጥቅም ላይ ማዋል አስተዋፅኦው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መሀመድ ዑስማን (ዶ/ር) በበኩላቸው÷በረሃማና ከፊል በረሃማ አካባቢዎችን ለማልማትና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረገ የጥናትና ምርምር ስራዎች ወሳኝ ናቸው ብለዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚቆየው ኮንፍረንስ ከአውሮፓ፣ ኤዥያ፣ ከአፍሪካ አህጉርና ከሀገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ አጥኚዎች የጥናት ፅሁፋቸው አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በሰማኸኝ ንጋቱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.