Fana: At a Speed of Life!

የቡድን 20 አባል ሀገራት ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቡድን 20 አባል ሀገራት ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ዓለም በገጠሟት ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ዙሪያ ለሁለት ቀናት የመከረው የቡድን 20 አባል ሀገራት ስብሰባ ተጠናቅቋል።

በመድረኩ ላይ የተሳተፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)÷ኢትዮጵያ በውሃ የኃይል ማመንጫ፣ በፀሐይ፣ በነፋስ እና የጂኦተርማል ኢነርጂ እምቅ አቅም ያላት ሀገረ መሆኗን ገልፀዋል፡፡

የቡድን 20 አባል ሀገራት ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉና በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ኃይል ዝርጋታ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

በአየር ንብረት ለውጥ፣ የበሽታ ወረርሽኝ እና በድህረ-ግጭት መልሶ ግንባታ ዙሪያ ሀገራት በትብብር መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያም በመድረኩ ገለልተኛ እና መርህ ተኮር አቋም በማንፀባረቅ ውጤታማ ተሳትፎ ማድረጓን በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.