Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በባሕርዳር ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በባሕር ዳር ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ዓለምአንተ አግደው፣ የባሕር ዳር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የሥራ ኀላፊዎቹ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የለውጥ ሥራዎች እንዲሁም የባሕርዳር ከተማ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።

በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እየተሠሩ ያሉ የለውጥ ሥራዎች ተስፋ ሰጪና የሚበረታቱ ናቸው መባሉን በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.