ማንቼስተር ዩናይትድ እና ኤቨርተን አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ መርሃ ግብር ኤቨርተን እና ማንቼስተር ዩናይትድ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያዩ።
ዛሬ 9፡30 ላይ በተካሄደ ጨዋታ የኤቨርተንን ግቦች ቤቶ በ19ኛው እንዲሁም ዱኮሬ በ33ኛው ደቂቃ ሲያስቆጥሩ ለማንቼስተር ዩናይትድ ቡርኖ ፈርናንዴዝ በ73ኛው እንዲሁም ማኑኤል ኡጋርቴ 80ኛው ደቂቃ አስቆጥሯል።
በከፍተኛ የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንቼስተር ዩናይትድ በሊጉ ካደረጋቸው 5 ተከታታይ ጨዋታዎች በሶስቱ ተሸንፎ በአንዱ አቻ እና አንድ አሸንፎ በ30 ነጥብ 15ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ኤቨርተን በበኩሉ በተከታታይ ካደረጋቸው የሊጉ ጨዋታዎች ሶስቱን አሸንፎ በሁለቱ አቻ በመውጣት በ31 ነጥብ 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።