ለስራ አጥ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር መንግሰታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በሐዋሳ ከተማ “ብቃት” የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የ2ኛ ዙር መዝጊያ እና የ3ኛ ዙርያ ትግበራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል።
የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በየነ ባራሳ በዚህ ወቅት ÷መንግስት ሥራ አጥ ዜጎችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ መንግታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በመተባበር እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በዚህ ፕሮጀክት ተቀጣሪ የሆኑ ወጣቶች ጠንክረው መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡
የሥና ክህሎት ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ በበኩላቸው÷መንግስት በቀዳሚነት ከያዛቸው አጀንዳዎች መካከል በከተሞች አከባቢ በስፋት የሚስተዋለውን የስራ አጥነት ቁጥር መቀነስ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በመደበኛ ሥራ ፈጠራ ከሚከናወነው ተግባራት ጎን ለጎን ከዓለም ባንክ ጋር የሚተገበረው ብቃት የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም አንዱ ስለመሆኑ መግለጻቸውን የክልሉ የሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡
የሥራ ዕድል ፈጠራ ያገኙ ወጣቶችም ከዕለት ጉርስ በላይ በሀገር ግንባታ ሂደት ሚናቸው የጎላና ለሌሎች ወጣቶች አርአያ መሆን እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።