የኢትዮጵያ የባህል ቡድን በ38ኛው ሱራጅኩንድ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ተሳተፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የባህል ቡድን በ38ኛው ሱራጅኩንድ ዓለም አቀፍ የሜላ 2025 የዕደ ጥበብ ፌስቲቫል ላይ ተሳተፈ።
የባህል ቡድኑ የኢትዮጵያን የባህል ብዝሃነት እና ልዩ ልዩ ቅርሶች ለዕይታ ማቅረቡ ተገልጿል።
ቡድኑ የሀገሪቱን ልዩ የባህል ማንነት የሚያጎሉ የአፍሪካን ባህላዊ ሙዚቃ፣ ውዝዋዜ እና ዕደ ጥበብ ያካተቱ ማራኪ ትዕይንቶች ለፌስቲቫሉ ታዳሚያን ማቅረቡን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ባህል ከማስተዋወቅ ባለፈ ዓለም አቀፍ ወዳጅነትን እና የኢትዮ-ህንድ ጥብቅ የባህል ትስስርን አጉልቶ ያሳዬ መሆኑ በመረጃው ተጠቅሷል።