በሐረሪ ክልል የህዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል የህዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው፡፡
በኮንፈረንሱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር እና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መላኩ አለበል፣ በብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል መሐመድ ሁሴን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
በመድረኩ ከተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች ለሚነሱ ጥያቄዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴና የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተሾመ ኃይሉ