Fana: At a Speed of Life!

በቦንጋ ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቦንጋ ከተማ የሕዝብ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አወሉ አብዲ፣ የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በኮንፈረንሱ ከተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች የሚነሱ ጥያቄዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.