ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት አሳድገዋል-አቶ መላኩ አለበል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገለጹ።
በሐረር ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሀገር አቀፍ የሕዝብ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እንዳሉት÷ ብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ያከናወናቸው የልማት፣ የሰላም፣ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ስራዎች ህዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ናቸው።
በተለይም ህዝብና መንግስትን በማስተባበር ሀገርን ማልማትና ማሻገር እንደሚቻል በግልጽ የታየበት መሆኑንም አመልክተዋል።
በሐረሪ ክልልም የተከናወኑ የልማት ስራዎች ነዋሪውን ተጠቃሚ ያደረጉና የህዝቡን የልማት ጥያቄ የመለሱ ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡