Fana: At a Speed of Life!

የናይል ተፋሰስ አባል ሀገራት ሚኒስትሮች የታላቁ ህዳሴ ግድብን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የናይል ተፋስስ ሀገራት ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶችና ጋዜጠኞች የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል።

 

በጉብኝቱ  የኬንያ፣ ታንዛኒያ፣ ኡጋንዳ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የኢትዮጵያ የውሃ ሚኒስትሮችን ጨምሮ  የተፋሰሱ ሀገራት ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል።

 

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር ኢ/ር) እና የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ክፍሌ ሆሮ ለሚኒስትሮቹ ገለፃ አድርገዋል።

 

“የናይል ትብብርን ማጎልበት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ለጋራ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል 19ኛው የናይል ቀን ትናንት መከበሩ ይታወቃል።

 

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.