መንግስት ለህዝቡ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነው-ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)መንግስት የህዝቡን ጥያቄ ለማድመጥ እና ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ።
በአሶሳ ከተማ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ህዝባዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል÷ መንግስት የህብረተሰቡን ጥያቄ ለማድመጥ እና ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነው ብለዋል።
በክልሉ የተገኘው ውጤት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እና ለሁለንተናዊ ብልጽግና መሳካት ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑንም ተናግረዋል።
ብልጽግና ፓርቲ የሚያከናውቸው ሁሉን አቀፍ ስራዎች ግቡ የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሆነም መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድር÷በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ያሻሻሉ ናቸው ያሉ ሲሆን አሁንም የመልካም አስተዳደር እና የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት የክልሉ መንግስት በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።