Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጀማል አህመድ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ የቢዝነስ መሪ ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ የቢዝነስ መሪ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

 

በሞሮኮ በተካሄደው የ2024 የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ አመራር ሽልማት ነው አቶ ጀማል አህመድ አሸናፊ መሆን የቻሉት፡፡

 

ሽልማቱ ኮርፖሬት ተቋማትን በልዩነት የመሩና የአፍሪካ የንግድ ገጽታን በመቀየር የላቀ ስኬቶችን ያስመዘገቡ መሪዎች የሚሸለሙበት መሆኑ ተነግሯል፡፡

 

አቶ ጀማል ለአሸናፊነት የበቁት በእርሳቸው አመራር ለሀገር እንዲሁም ለማህበረሰቡ በጎ ስራዎች በመሰራቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.