Fana: At a Speed of Life!

ፓርቲው ኅብረ ብሔራዊነትን ባከበረ መልኩ ሀገረ መንግሥትን ለመንገባት የጀመረው ሂደት ውጤታማ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ብልጽግና ፓርቲ ኅብረ ብሔራዊነትን ባከበረ መልኩ ሀገረ መንግሥትን ለመንገባት የጀመረው ሂደት ውጤታማ መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይ ገለጹ።

 

በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው የሕዝብ ኮንፈረንስ የተሳተፉት አቶ ይርጋ ሲሳይ÷ብልጽግና ፓርቲ ሁሉንም አክብሮና አሳትፎ እውነተኛ መንገድ ይዞ እየተጓዘ ያለ ትልቅ ፓርቲ ነው ብለዋል።

 

ሁሉም አንድ ሆነው ተባብረው ሠርተው የሚኖሩባት ጠንካራ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት እየሠራ ያለ ፓርቲ መሆኑንም ተናግረዋል።

 

ፓርቲው የሕዝብ ኃላፊነት ተሸክሞ ወደ ተግባር ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ብዙ ተግዳሮቶች ቢገጥሙትም ፈተናዎችን ወደ መልካም ዕድል እየቀየረ በርካታ ስኬቶችን እያስመዘገበ መምጣቱን ገልጸዋል።

 

በሁሉም ዘርፎች ወደ አገልግሎት የገቡና በግንባታ ሂደት ላይ የሚገኙ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ለኢትዮጵያ ብልጽግና መስፈንጠሪያ መሆናቸውን አንስተዋል።

 

በፖለቲካ ዘርፍ አሰባሳቢ ትርክቶች መምጣቸውን ጠቅሰው ፓርቲው ቃሉን አክብሮ የሚፈጽም በመሆኑ በሁለተኛ መደበኛ ጉባዔው የተቀመጡ ውሳኔዎችንም በተግባር ያረጋግጣል ብለዋል።

 

ፓርቲው ሕዝቡን እንደ ትልቅ አቅም ተጠቅሞ አሳታፊ በሆነ መልኩ የሚሠራ መሆኑን መናገራቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.